ስለ ሮክስ (Roks)

ስለ ሮክስ (Roks)

ስለ ሮክስ

 ሮክስ በስዊድን የሚገኝ ብሄራዊ የሴቶችና ወጣት ሴቶች መጠለያ ድርጅት ነው። በሀገሪቱ ወስጥ ከሚገኙት ትልቁ የሴቶችና ወጣት ሴቶች መጠለያ ነው፡፡ሮክስ አላማዎች በመጠለያው በጋራ ፍላጎቶች አማካኝነት በሴቶች ላይ ለሚደርሰው የወንዶች ጥቃት እንዳይደርስ ጥበቃ ለማድረግ ነው፡፡ ሮክስ ሕዝባዊ ሀሳቦችን ይቀርጻል። መጠለያው የሚጋፈጣቸውን ነገሮች ለህዝብ ያሳውቃል፥ መጠለያውን የሚመለከቱ ጉዳዮችን ይመረምራል፡፡ አሁን በድርጅቱ 100 የሚጠጉ ሴቶችና ወጣት ሴቶች ይገኛሉ፡፡ ሮክስ በሴቶች ጉዳይ ላይ የሚንቀሳቀስ ድርጅት ሲሆን ተግባሩም በሴቶችና ወጣት ሴቶች መብቶችና ነጻነት ላይ እንዲሁም በሁሉምእኩልነት ደረጃ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡

 

የሴቶቹ መጠለያዎች

እያንዳንዱ መጠለያ ራሱን የቻለና በራሱ መንገድ የሚሰራ ነው፡፡ ያም ሆኖ ሁሉም መጠለያዎች ሴቶችና ወጣት ሴቶች እርዳታ ሲፈልጉ የድንገተኛ እርዳታ ስልክ ጥሪ ማድረግ የሚችሉበትስልክ መስመር አለ፡፡ ደዋዮች ማንነታቸውን ለመግለጽ አይገደዱም። የደወለም አይመዘገብም፡፡

የሴቶቹ መጠለያ የተገልጋዮችን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ድጋፍ ይሰጣል፡፡ ምን አልባት ስላለችበት ሁኔታና ስለ ግንኙነት ልታወራ ትችላለች፡፡ ለፖሊስ ሪፖርት ማድረግ ወይም የአሳዳጊነት ሙግት ምክር ልትፈልግ ትችላለች፡፡ አሁን ወይም ከብዙ አመታት በፊት የጾታ ጥቃት የደረሰባት ልትሆን ትችላለች፡፡ ለዚህም በመጠለያው የሚሰሩ ሴቶች ድጋፍና ምክሮችን ይለግሳሉ። ለምሳሌ ወደ ፖሊስ፣ ወደ ጠበቃና ወደ ማህበራዊ አገልግሎት ሰጪዎች መሄድን በተመለከተ ድጋፍ ያደርጋሉ፡፡ አብዛኛዎቹ መጠለያዎች ለባለጉዳይ ሴቶቹና ለልጆቻቸው መጠለያ ያቀርባሉ፡፡

ብዛት ያላቸው መጠለያዎች ህጋዊ ሆስቴል ተብለው ተለያይተዋል፡፡ ጥቂት መጠለያዎች የመስማት ችግር ላለባቸው ሴቶች የጽሁፍ ስልክ መጠቀሚያ አላቸው፡፡ ሌሎች መጠለያዎች ከቅርብ ዘመድ ጋር ስለተደረጉ ጾታዊ ግንኙነቶች በተመለከተ ለማስተናገድ ተብለው በልዩ ሁኔታ የተዘጋጁ ናቸው፡፡ 

የሴቶች መጠለያን እዚህ ጋር ያግኙ

 

የወጣት ሴቶች መጠለያ

በሮክስ 30 ያህል የወጣት ሴቶች መጠለያዎች ሲኖሩ ከነዚህ ውስጥም አስር ያህሉ ገለልተኛ ድርጅቶች ናቸው፡፡ የወጣት ሴቶች መጠለያው ልክ እንደ ሴቶች መጠለያው በተመሳሳይ መንገድ የሚሰራ ሆኖ ነገር ግን ለወጣት ሴቶች የተባለ ሲሆን ለምሳሌ ማስፈራራት፣ ማጎሳቆልና የፆታ ጥቃትን ወይም በሌላ ምክንያት፣ ሌሎች ልጃገረዶችን ማነጋገርን በተመለከተ ይሰራል፡፡ እንዲሁም ልጃገረዶቹ በመጠለያው የሚገኙበትን ሁኔታ ለህዝብ ግንዛቤ ለማስጨበጥ በንቃት ይሰራል፡፡ የወጣት ሴቶቹ መጠለያዎች ድረገጽ  አላቸው፡፡ ይህም የሚከተለው ነው። www.tjejjouren.se

የወጣት ሴቶችን መጠለያ እዚህ ጋር ያግኙ

 

በመጠለያው መስራት

በመጠለያው የሚሰሩ አብዛኞቹ የበጎ ፈቃድ አገልጋዮች ናቸው፡፡ በመጠለያው ተቀባይነትን ለማግኘት መጀመሪያ በመጠለያው በሚዘጋጀው የጥናት ክበብ ላይ መሳተፍ ያስፈልጋል፡፡ የሰራተኛ አባል ለመሆን ከፈለጉ በአካባቢዎ የሚገኘውን የሴቶች ወይም ልጃገረዶች መጠለያ ያግኙ፡፡